የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንግዶቹን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገለፀ!

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንግዶቹን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው እንዲመጡ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ እንግዶቹን ለመቀበል የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል አስታውቀዋል ።

በዚሁ መሰረት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ/Ethiopian origin ID/ የታደሰም ሆነ የአገልግሎት ግዜው ያለፈበት፣ በልዩ ሁኔታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያለ ቪዛ ወደ ኢትዮጵያ መግባት የሚቻል መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ የታደሰንም ሆነ ግዜው ያለፈበትን መታወቂያ ኤርፖርት በኢሚግሬሽን ካውንተር ላይ ተጓዦች ስለሚጠየቁ መያዝ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በሌላ በኩል የሌላ ሃገር ፓስፖርት የያዙና የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ /Ethiopian origin ID/ አገልግሎት ለማግኘት የሚፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የፓስፖርት እድሳት አገልግሎት ከፈለጉ አስፈላጊ ሰነዶችን በማዘጋጀት http://xn--www-86o.digitalinvea.com/ ድህረ ገጽ ላይ ማመልከት የሚችሉ ሲሆን፣ ተቋሙ በተለየ መልኩ ከ15 ቀን ባልበለጠ ግዜ ውስጥ ተጓዦች በሞሉት አድራሻ በመላክ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።ከዚህ በፊት የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ያሌላቸው ደንበኞች የቪዛ አገልግሎት ለማግኘት በ www.evisa.gov.et ድህረ ገጽ ላይ ማመልከት የሚችሉ ሲሆን፣ በሂደቱ ለሚገጥማቸው ማንኛውም ችግሮች support@evisa.gov.et በሚለው የተቋሙ የኢሜል አድራሻ ላይ ጥያቄ ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ጥሪ በተደረገበት የጊዜ ገደብ ውስጥ ወደ ሀገር ቤት ለሚገቡ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የመዳረሻ ቪዛ/on arrival visa/ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ በኤርፖርት ላይ የሚቆዩትን ግዜና ድካም መቀነስ እንዲቻል በኦንላይን ቀድሞ ቢያመለክቱ የሚበረታታ እንደሆነ መግለጻቸውን አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል። የቪዛ ጥያቄ በተቋሙ ህጋዊ ድህረ ገጽ www.evisa.gov.et ላይ ቢቻ ሲቀርብ አገልግሎቱን የሚሰጥ መሆኑንን ተቋሙ አሳስቧል።

ከዚህ ቀደም በሌሎች ገጾች ላይ ጥያቄ እንደሚቀርብና ተገልጋዮች እንደሚጭበረበሩ መገንዘቡን የገለጸው ተቋሙ እስከአሁን የተደረሰባቸው ገጾች www.ethiopiaevisa.comwww.ethiopiaonlinevisa.com እና www.evisaforethiopia.com በመሆናቸው እነዚህ አድራሻዎች የተቋሙ አለመሆናቸውን አስታዉቋል።

Facebook
Twitter
Telegram
WhatsApp

Related Content

Frequently Asked Questions (FAQ)s

People having an Ethiopian Origin ID, whether active or expired, are not required to obtain a visa to enter Ethiopia. Others should apply for a visa online or apply for a visa on arrival.

Passengers must present a medical certificate showing a negative COVID-19 test result before boarding a flight to Ethiopia. The test should be taken at most 120 hours before arrival.

People with Ethiopian Origin ID either active or expired can enter to Ethiopia with out visa. But they need to show either the active or the expired Ethiopian Origin ID at the airport counters. 

Ethiopian that hold non-Ethiopian passport can apply for Ethiopian origin ID online. It will be processed within 15 Days.

Please visit https://www.moh.gov.et/site/Donation_For_Health_Facility_Restoration for Steps and Procedures to Facilitate Donations of Medicines, Medical Supplies and Equipment For Health Facility Restoration.

Please visit respective hotels website to book your hotels

Please check our website for the list of tour operators that offer discount of up to 30%.

Get in touch with us

We are here to help!