“Back to your origins” የሚል ስያሜ የተሰጠው የሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ጥሪ በሶስት ዙሮች የሚኪያሄድ ነው::በዚህ መሰረት:
➢ የመጀመሪያው ዙር፡ Connect to Your Multi-Cultural Roots (ከብዝኃ ባህል መሰረትዎ ጋር ይገናኙ)
ከታህሳስ 20 እስከ ጥር 30 ይካሄዳል::
➢ ሁለተኛው ዙር Connect to Your Historical Roots (ታሪካዊ መሰረትዎን ይወቁ) ከየካቲት 20 እስከ ሚያዝያ 30 ይካሄዳል::
➢ ሶስተኛው ዙር Leave your Legacy, savor your holiday (አሻራዎን ያኑሩ፣የእረፍት ጊዜዎን ያጣጥሙ) ከሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል::
ሚንስትሯ ጥሪው የተደረገው በውጭ የተወለዱ ኢትዮጵያውያን የሀገር ፍቅር ስሜታቸው እንዲዳብር እና ከአገራቸው ጋር ያላቸው ትስስር እንዲጠናከር ለማስቻል መሆኑን አንስተዋል።
ጥሪውን ተቀብለው ለሚመጡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ትኬት ቅናሽ የሚደረግላቸው ሲሆን
ሆቴሎች፣ አስጎብኝ ድርጅቶች የትራስፖርት አገልግሎት አቅራቢዎች ልዩ የዋጋ ቅናሽ አድርገው ለማስተናገድ መዘጋጀታቸውን አምባሳደር ናሲሴ ገልፀዋል::
የተቀላጠፈ የጉምሩክና ኢሚግሬሽን አገልግሎቶች ለመስጠት የሚያችሉ
ሁኔታዎችም ተመቻችተዋል፡፡
ከሀገራቸው ጋር ያላቸውን ትስስር የሚያጠናክሩ የተለያዩ ሁነቶች እንደሚዘጋጅላቸውም ገልፀዋል::